ስራዎቻችን
የጤና መረጃ ማቅረብ
በአሁኑ ወቅት ምርኩዝ ከጤና ጋር የተገናኙ መረጃዎችን በዋናነት በተለያዩ የካንሰር አይነቶች እና ቀሪ የህይወት ዘመናቸው ከስድስት ወር በታች ለሆኑ ግለሰቦች የህይወት መጨረሻ እንክብካቤን አሰጣጥ ላይ ያተኮሩ መረጃዎችን በመስጠት ላይ ይገኛል። ይህ ጠቃሚ የጤና መረጃ በዋነኛነት የሚሰራጨው እንደ ድረ-ገፃችን፣ ዩቲዩብ ቻናላችን፣ ፌስቡክ ፣ ቲክቶክ ፣ ሊንክደን እና ትዊተር ባሉ ማህበራዊ ሚዲያ/ዲጂታል መድረኮች ነው። ብዙ ተመልካቾችን ለማግኘት እና ተደራሽነታችንን ለማስፋት ግብአቶችን በእነዚህ መድረኮች ለማቅረብ እንተጋለን ።
በጎ አድራጎት
እኛ ምርኩዞች እያንዳንዱ የካንሰር ታማሚ የመክፈል አቅሙ ሁኔታ ምንም ይሁን ምን አለ ይተባለውን ምርጥ የጤና እንክብካቤ ማግኘት እንዳለበት አጥብቀን እናምናለን። የሕክምና ወጪዎች የፋይናንስ ጫና አዳካሚ ሊሆኑ እንደሚችሉ ስለምንገነዘብ የእርዳታ እጃችንን ለማቅረብ እዚህ ተገኝተናል። ማንም ሰው ካንሰርን በሚዋጋበት ጊዜ ተጨማሪ የገንዘብ ችግር እንዳይገጥመው ለመርዳት እንጥራለን።
በለጋሾቻችን እና በጎ ፈቃደኞቻችን ቸር ድጋፍ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው የካንሰር ህሙማን የተለያዩ የጤና እንክብካቤ ወጪዎችን ለመሸፈን የገንዘብ ድጋፍ እንሰጣለን። ይህ ድጋፍ የሚከተሉትን ያጠቃልላል ፤ ነገር ግን አይወሰንም፡፡
- የመድሃኒት ወጪዎች
- የሆስፒታል ማረፊያ ወጪዎች
- ምርመራ እና ሌሎች የሂደቱ ወጪዎች
ለውጥ ለማምጣት ይቀላቀሉን!
የእርስዎ አስተዋፅዖ መጠኑ ምንም ያህል ይሁን በሚያስፈልጋቸው የካንሰር ሕሙማን ሕይወት ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ሊያሳድር ይችላል። አላማችንን ለመደገፍ እና ለመሳተፍ ጥቂት መንገዶች እኚህን ይመስላሉ
የገንዘብ ልገሳ
የእርስዎ ልገሳ በቀጥታ በገንዘብ እጦት ለሚታገሉ የካንሰር ህሙማን የጤና እንክብካቤ ወጪዎችን ለመሸፈን ይረዳል። እያንዳንዱ ብር ለውጥ ለማምጣት ይጠቅማል!
ገንዘብ ማሰባሰብ
የበጎ አድራጎት ሩጫዎች፣ የሽያጭ ባዛሮችን ወይም የማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻዎችን የመሳሰሉ የገንዘብ ማሰባሰቢያ ዝግጅቶችን በማደራጀት ገንዘብ ለማሰባሰብ እና ለሁሉም የካንሰር ህሙማን ተደራሽ የጤና እንክብካቤ አስፈላጊነት ግንዛቤን በማስፋት ሊያግዙ ይችላሉ።
የማህበራዊ ሚዲያ
በምናደርጋቸው እንቅስቃሴዎችች ላይ ወቅታዊ መረጃ ለማግኘት እና ተልእኳችንን ከጓደኞችዎ እና ከቤተሰብዎ ጋር ለመጋራት በማህበራዊ ሚዲያ መድረኮች ላይ ይከተሉን። መልእክታችንን በማጉላት፣ ብዙ ተመልካቾችን እንድናገኝ እና የበለጠ ድጋፍ እንድናገኝ ይረዱናል።
በጎ ፈቃደኞች
ርህሩህ የበጎ ፈቃደኞች ቡድናችንን ይቀላቀሉ እና የካንሰር ህሙማን ለመርዳት ችሎታዎን እና ጊዜዎን ይስጡ። ከአስተዳደራዊ ተግባራት እስከ ዝግጅቶችን ማደራጀት፣ የእርስዎ አስተዋጽዖ በዋጋ ሊተመን የማይችል ይሆናል።
አላማችንን ለመደገፍ እና ለመሳተፍ ምልክቱን ይጫኑ
የእርስዎ አስተዋፅዖ መጠኑ ምንም ያህል ይሁን በሚያስፈልጋቸው የካንሰር ሕሙማን ሕይወት ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ሊያሳድር ይችላል።