የልግሳ አማራጮች

የእርስዎ አስተዋፅዖ መጠኑ ምንም ያህል ይሁን በሚያስፈልጋቸው የካንሰር ሕሙማን ሕይወት ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ሊያሳድር ይችላል።  አላማችንን ለመደገፍ እና ለመሳተፍ ጥቂት መንገዶች እኚህን ይመስላሉ

የገንዘብ ልገሳ

የእርስዎ ልገሳ በቀጥታ በገንዘብ እጦት ለሚታገሉ የካንሰር ህሙማን የጤና እንክብካቤ ወጪዎችን ለመሸፈን ይረዳል። እያንዳንዱ ድጋፍ ለውጥ ለማምጣት ይጠቅማል!

የማህበራዊ ሚዲያ

በምናደርጋቸው እንቅስቃሴዎችች ላይ ወቅታዊ መረጃ ለማግኘት እና ተልእኳችንን ከጓደኞችዎ እና ከቤተሰብዎ ጋር ለመጋራት በማህበራዊ ሚዲያ መድረኮች ላይ ይከተሉን። መልእክታችንን በማጉላት፣ ብዙ ተመልካቾችን እንድናገኝ እና የበለጠ ድጋፍ እንድናገኝ ይረዱናል።

ገንዘብ ማሰባሰብ

የበጎ አድራጎት ሩጫዎች፣ የሽያጭ ባዛሮችን ወይም የማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻዎችን የመሳሰሉ የገንዘብ ማሰባሰቢያ ዝግጅቶችን በማደራጀት ገንዘብ ለማሰባሰብ እና ለሁሉም የካንሰር ህሙማን ተደራሽ የጤና እንክብካቤ እና አስፈላጊውን ግንዛቤን በማድርስ ሊያግዙን ይችላሉ።

በጎ ፈቃደኞች

ርህሩህ የበጎ ፈቃደኞች ቡድናችንን ይቀላቀሉ እና የካንሰር ህሙማን ለመርዳት ችሎታዎን እና ጊዜዎን ይስጡ። ከአስተዳደራዊ ተግባራት እስከ ዝግጅቶችን ማደራጀት፣ የእርስዎ አስተዋጽዖ በዋጋ ሊተመን የማይችል ይሆናል።

አላማችንን ለመደገፍ እና ለመሳተፍ ምልክቱን ይጫኑ

የእርስዎ አስተዋፅዖ መጠኑ ምንም ያህል ይሁን በሚያስፈልጋቸው የካንሰር ሕሙማን ሕይወት ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ሊያሳድር ይችላል።

Scroll to Top