ካንሰር ምንድን ነው

ካንሰር የተወሰኑ በሰውነት ውስጥ ያሉ ህዋሶች ከቁጥጥር ውጭ በሆነ መንገድ አድገው ወደ ሌሎች የሰውነት ክፍሎች የሚተላለፉበት በሽታ ነው።

ካንሰር በሰውነት ውስጥ በማንኛውም ቦታ ሊጀምር ይችላል። የሰው ልጅ ህዋሶች በመደበኛነት ያድጋሉ ፣ ይባዛሉ እና አስፈላጊ የሁኑ አዳዲስ ሴሎችን ይፈጥራሉ። ሴሎች ሲያረጁ ወይም ሲጎዱ ይሞታሉ እና አዲስ ሴሎች ይተካሉ፡፡ ይህ ሥርዓት ያለው ሂደት ሳይሳካ ሲቅር ወይም ሲበላሽ ያልተለመዱ ወይም የተበላሹ ሕዋሶች ያድጋሉ እና በማይገባቸው ጊዜ ይባዛሉ። እነዚህ ህዋሶች ዕጢዎችን የመፍጠር አቅም አላቸው፡፡ ዕጢዎቹ የካንሰር ህዋሶች የያዙ ሊሆኑ ወይም ላይሆኑ ይችላሉ፡፡ የእያንዳንዱ ሰው ካንሰር ልዩ የሆነ የዘረ መል ለውጦች ጥምረት አለው እናም ካንሰሩ እያደገ ሲሄድ ብዙ ለውጦች ይከሰታሉ፤ በተመሳሳይ ዕጢ ውስጥ እንኳን የተለያዩ ህዋሶች ፤ የተለያዩ የጄኔቲክ ለውጦች ሊከሰት ይችላል፡፡ የካንሰር እጢዎች በአቅራቢያ ያሉ ሕብረ ሕዋሳትን ይወርራሉ እና በሰውነት ውስጥ ወደ ተለያዩ ቦታዎች በመስፋፋት አዳዲስ ዕጢዎችን ይፈጥራሉ፡፡

ካንሰር የዘረመል በሽታ ነው ፤ ህዋሶቻችን እንዴት እንደሚሠሩ በተለይም እንዴት እንደሚያድጉ እና እንደሚከፋፈሉ በሚቆጣጠሩት ዘረመሎች ላይ ለውጦች ይከሰታል። ከዘር በተጨማሪ እንደ ማጨስ ፣ የአኗኗር ዘይቤዎች እና ለጨረር መጋለጥ አንድ አንድ ለካንሰር ሊያጋልጡ የሚችሉ እና ሊወገዱ የሚችሉ አጋላጭ ምክንያቶች ናቸው።

ካንሰር ውስብስብ በሽታ ነው፡፡ የበሽታው ምልክቶች ሳይታዩ ለዓመታት ሊኖሩ ይችላሉ፤ ሌላ ጊዜ ደግሞ ካንሰር በፍጥነት እየተባባሱ የሚታዩ ምልክቶችን ሊያመጣ ይችላል። ብዙ የካንሰር ምልክቶች ከሌሎች አነስተኛ የበሸታ ምልክቶች ጋር መመሳሰል ሊኖራቸው ይችላል።

የጤና ባለሙያዎች ህክምናን ለማቀድ እና ለሚመጣው ውጤት ለማዘጋጀት በሰውነት ላይ በተከሰቱ ለውጦች ላይ በመመስረት የካንሰር ደረጃዎችን ያወጣሉ። ቀደም ብሎ ማወቅና እና አዳዲስ ሕክምናዎች ካንሰርን እየፈወሱ እና ካንሰር ያለባቸው ሰዎች ረጅም ዕድሜ እንዲኖሩ እየረዳቸው ነው።

አምዶች

የጉበት ካንሰር

የጉበት ካንሰር የጉበት ካንሰር (ሄፓቲክ ካንሰር) በመባል የሚታወቀው በጉበት ህዋሶችውስጥ የሚጀምር የካንሰር አይነት ነው። ጉበት በሆዱ የላይኛው ቀኝ በኩል...

አላማችንን ለመደገፍ እና ለመሳተፍ ምልክቱን ይጫኑ

የእርስዎ አስተዋፅዖ መጠኑ ምንም ያህል ይሁን በሚያስፈልጋቸው የካንሰር ሕሙማን ሕይወት ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ሊያሳድር ይችላል።

Scroll to Top