ርህራሄ የተሞላበት እንክብካቤ

የጤና መረጃ

በአሁኑ ወቅት ምርኩዝ ከጤና ጋር የተገናኙ በዋናነት በተለያዩ የካንሰር አይነቶች እና ቀሪ የህይወት ዘመናቸው ከስድስት ወር በታች ለሆኑ ግለሰቦች የህይወት መጨረሻ እንክብካቤን አሰጣጥ ላይ ያተኮሩ መረጃዎችን በመስጠት ላይ ይገኛል።

በጎ አድራጎት

ምርኩዝ እያንዳንዱ የካንሰር ታማሚ የመክፈል አቅሙ ሁኔታ ምንም ይሁን ምን አስፈላጊ የሆነውን የጤና እንክብካቤ ማግኘት እንዳለበት አጥብቀን እናምናለን። ማንም ሰው ካንሰርን በሚዋጋበት ጊዜ ተጨማሪ የገንዘብ ችግር እንዳይገጥመው ለመርዳት እንጥራለን።

ህይወት ላይ እናተኩር

የመጨረሻ ቀናት እንክብካቤ

ይህ የህክምና አይነት የፅኑ ህሙማንን ስቃይ ለመቀነስ እና መንፈሳዊ እና አእምሯዊ ድጋፍ ለመስጠት፣ ከፈውስ በላይ ቀሪ ሂወትን ምቹ እና ከስቃይ የፀዳ ለማድረግ የሚሰጥ ድጋፍ ነው::

ይህ የህክምና ድጋፍ እንደ ካንሰር አይነት በማይድን በሽታ ለሚሰቃዩ እና ቀን ለተቆረጠላቸው ሰዎች ርኅራኄ የተሞላው እንክብካቤ በመስጠት ቀሪ የሕይወት ዘመንን በምቹ እና ምሉዕ ማድረግ ላይ ያተኩራል::

ስለ ምርኩዝ

ምርኩዝ እ.ኤ.አ. በ 2023 በተለያየ የሙያ ዘርፍ ውስጥ ያሉ ፣ ከጤና ባለሙያ እስከ ሥራ ፈጣሪ ድረስ ሰፊ የሙያ ልዩነት ነገር ግን አንድ አይነት ራእይ ባላቸው ግለሰቦች የተቋቋመ ማህበር ሲሆን ዓላማውም ለካንሰር በሽተኞች እንክብካቤ እየሰጡ ላሉ ግለሰቦች እና ቤተሰቦች በመረጃ ላይ የተመሰረተ የህክምና ውሳኔ ላይ እንዲደርሱ ማስተማር ፣ ማበረታታት እና መርዳት ነው። ሁሉም ሰው ልዩ የሆነ አካላዊ ፣ ስሜታዊ እና መንፈሳዊ ፍላጎቱን የሚያሟላ ተገቢውን የካንሰር ህክምና እና እንክብካቤ ማግኘት እንዳለበት እናምናለን፡፡ አላማችንም የካንሰር ህሙማን እና ተንከባካቢዎቻቸው በዚሀ አስቸጋሪ ጊዜ ውስጥ ሲያልፉ አስፈላጊውን እውቀት የሚያገኙበት፣ መረጃ እና ልምድ የሚለዋወጡበት እና እርስ በርስ የሚደጋገፉበት ቤተሰባዊ መድረክ መገንባት ነው።

ታሪካችን

ለየሸዋሉል ተሰማ መታሰቢያ ተወዳጅ አባት ፣ ባል እና ጓደኛ ከ19 43 - 2014 ዓ.ም

የሁለቱ መስራች አባሎቻችን አባት የሆነው የሸዋሉል ተሰማ በ2022/2014 ነበር ወደ ጉበቱ የተሰራጨ የቆሽት(ጣፍያ) ካንሰር እንዳለበት የታወቀው ። የሚወዱትን ሰው ልክ አብዛኛዎቹ የካንሰር ህሙማን ላይ በሚታየው ፍጥነት እየደክሙ ሲመጡ መመልከት በጣም ከባድ ቢሆንም እንዴት መርዳት እንዳለቦት ካለማወቅ የሚመጣው ተስፋ ቢስነት ጉዳዩን የበለጠ ከባድ ያደርገዋል። የየሸዋሉል ቤተሰቦች የጤና ባለሞያ ከመካከላቸው በመኖሩና የበሽታውን ባህሪ ስለሚያውቁ እና ለሰዓታት የሚፈጅ ጥናት በበኩላቸው ስላደረጉ ብዙም አልታገሉም። ይህን ክፍተት ባስተዋሉበት ጊዜ ነበር  በኢትዮጵያ ውስጥ ስለ ካንሰር እና የካንሰር ህሙማንን እንዴት መንከባከብ እንደሚቻል የመረጃ እጥረት እንዳለ መገንዘብ የቻሉት::

አምዶች

ፕሮስቴት ካንሰር

የፕሮስቴት ካንሰር ውስብስብ በሽታ ሲሆን ትክክለኛ መንስኤዎቹ ገና ሙሉ በሙሉ አልተረዱም ይሁን እንጂ ተመራማሪዎች አንድ ወንድ በፕሮስቴት ካንሰር የመያዝ እድልን የሚጨምሩ በርካታ የአደጋ መንስኤዎችን ለይተው አውቀዋል…

የጉበት ካንሰር

የጉበት ካንሰር (ሄፓቲክ ካንሰር) በመባል የሚታወቀው በጉበት ህዋሶችውስጥ የሚጀምር የካንሰር አይነት ነው። ጉበት በሆዱ የላይኛው ቀኝ በኩል የሚገኝ ወሳኝ አካል ነው ደምን ከስርአተ ልመት ሥርዓት ውስጥ የማጣራት እና የማቀነባበር እንዲሁም ለምግብ መፈጨት የሚረዳንን ሃሞት የማምረት ሃላፊነት አለበት…

የደም ካንሰር

የደም ካንሰር የደም እና የአጥንት መቅኒ ላይ ተጽእኖ የሚያሳድር የካንሰር አይነት ነው። የደም ካንሰር የደም ሴሎችን የሚያመነጩ ሕብረ ሕዋሳት የሆኑትን የደም እና የአጥንት መቅኒ የሚጎዳ የካንሰር አይነት ነው። በደም ካንሰር  ያልተለመዱ እና በትክክል የማይሰሩ ነጭ የደም ህዋሶች …

አላማችንን ለመደገፍ እና ለመሳተፍ ምልክቱን ይጫኑ

የእርስዎ አስተዋፅዖ መጠኑ ምንም ያህል ይሁን በሚያስፈልጋቸው የካንሰር ሕሙማን ሕይወት ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ሊያሳድር ይችላል።

Scroll to Top