ታሪካችን

ምርኩዝ እ.ኤ.አ. በ 2023 በተለያየ የሙያ ዘርፍ ውስጥ ያሉ ከ ጤና ባለሙያ እስከ ሥራ ፈጣሪ ድረስ ሰፊ የሙያ ልዩነት ነገር ግን አንድ አይነት ራእይ ባላቸው ግለሰቦች የተቋቋመ ማህበር ሲሆን ዓላማውም ሰዎችን ለመርዳት ነው።

የሁለቱ መስራች አባሎቻችን አባት የሆነው የሸዋሉል ተሰማ በ2022/2014 ነበር ወደ ጉበቱ የተሰራጨ የቆሽት(ጣፍያ) ካንሰር እንዳለበት የታወቀው ። የሚወዱትን ሰው ልክ አብዛኛዎቹ የካንሰር ህሙማን ላይ በሚታየው ፍጥነት አቅማቸው ሲደክም መመልከት በጣም ከባድ ቢሆንም እንዴት መርዳት እንዳለቦት ካለማወቅ የሚመጣው ተስፋ ቢስነት ጉዳዩን የበለጠ ከባድ ያደርገዋል። የየሸዋሉል ቤተሰቦች የጤና ባለሞያ ከመካከላቸው በመኖሩና የበሽታውን ባህሪ ስለሚያውቁ እና ለሰዓታት የሚፈጅ ጥናት በበኩላቸው ስላደረጉ ብዙም አልተቸገሩም። ይህን ክፍተት ባስትዋሉበት ጊዜ ነበር በኢትዮጵያ ውስጥ ስለ ካንሰር እና የካንሰር በህሙማንን እንዴት መንከባከብ እንደሚቻል የመረጃ እጥረት እንዳለ መገንዘብ የቻሉት:: ይሄን አስቸጋሪ ወቅት ህሙማን እና ተንከባካቢዎቻቸው ብዙም ሳይቸግሩ ማለፍ ይችሉ ዝንድ እንዲሁም ሰዎች ስለ ካንሰር እና ስለ ካንሰር ታካሚዎች የመጨረሻ ቀናት እንክብካቤ ፣ ለታካሚው ምን መደረግ እንዳለበት እና ቤተሰብ ፣ ጓደኛ ወይም ተንከባካቢ ህሙማንን ሲንከባከቡ ምን ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው ለማወቅ የሚመጡበት ቦታ እንዲሆን ታስቦ ፍላጎት ባላቸው ግለሰቦች እርዳታ ምርኩዝ እውን ሆነ ።

ለየሸዋሉል ተሰማ መታሰቢያ ተወዳጅ አባት ፣ ባል እና ጓደኛ ከ1943 - 2014 ዓ.ም

አላማችንን ለመደገፍ እና ለመሳተፍ ምልክቱን ይጫኑ

የእርስዎ አስተዋፅዖ መጠኑ ምንም ያህል ይሁን በሚያስፈልጋቸው የካንሰር ሕሙማን ሕይወት ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ሊያሳድር ይችላል።

Scroll to Top