የመጨረሻ ቀናት እንክብካቤ

ይህ የህክምና አይነት የፅኑ ህሙማንን ስቃይ ለመቀነስ እና መንፈሳዊ እና አእምሯዊ ድጋፍ ለመስጠት፣ ከፈውስ በላይ ቀሪ ሂወትን ምቹ እና ከስቃይ የፀዳ ለማድረግ የሚሰጥ ድጋፍ ነው::
ይህ የህክምና ድጋፍ እንደ ካንሰር አይነት በማይድን በሽታ ለሚሰቃዩ እና ቀን ለተቆረጠላቸው ሰዎች ርኅራኄ የተሞላው እንክብካቤ በመስጠት ቀሪ የሕይወት ዘመንን በምቹ እና ምሉዕ ማድረግ ላይ ያተኩራል::

ተከታታይነት ያለው የቤት ውስጥ እንክብካቤ

በዋነኝነት በቤተሰብ እና በልብ ወዳጆች የሚሰጥ እንክብካቤ ሲሆን በጤና ባለሙያ ደሞ ወቅታዊ የሆነ ክትትልን ያካትታል::

በባለሙያ የታገዘ ተከታታይ የቤት ውስጥ ሕክምና

ይህ ደግሞ በከፍተኛ ስቃይ ላይ ሆነው በሕክምና ተቋም ውስጥ ለመቆየት ፍላጎት ለሌላቸው ሰዎች በቤታቸው ሆነው በባለሙያ የታገዘ እንክብካቤ የሚሰጥበት ደረጃ ነው::

የተኝቶ ታካሚ አገልግሎት

ስቃዩ በቤት ውስጥ በሚደረግ እንክብካቤ መቆጣጠር የማይቻል ሲሆን ወደ ጤና ተቋም ተወስደው እንክብካቤውን ያገኛሉ::

የእረፍት እንክብካቤ

ተንከባካቢዎችን እረፍት ለመስጠት ታማሚው ተቋም ውስጥ ገብቶ ለአጭር ጊዜ ድጋፍ የሚያገኙበት መንገድ ነው::

አላማችንን ለመደገፍ እና ለመሳተፍ ምልክቱን ይጫኑ

የእርስዎ አስተዋፅዖ መጠኑ ምንም ያህል ይሁን በሚያስፈልጋቸው የካንሰር ሕሙማን ሕይወት ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ሊያሳድር ይችላል።

Scroll to Top